top of page

አድዋ

  • Writer: nejatahmedjuhar
    nejatahmedjuhar
  • May 14, 2019
  • 1 min read

ስለ አድዋ ብዙ ተብሏል... ይባላልም! አድዋ የአፍሪካውያንም ድል ነው! ተብሏል፣ ይባላልም ....እውነት ነዋ።

የአድዋ ድል በየአመቱ ሲከበር አንድ የማረሳት ገጠመኝ አለችኝ እስኪ ላጫውታቹ....

በቱርክ ሀገር የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ስትማሩ ፣ የትም ይሁን የት ስለ 'አታ ቱርክ ሙስጠፋ' ታሪክ መማር ግዴታ ነው። እኔ የምማርበት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዋች በተለየ መልኩ፣ ከውጭ ሀገር ለመጡ ተማሪዋች "ስፔሻል ክላስ" ያዘጋጃል። ይህም ማለት፦ ስለ ቱርክ, በተለይ ደግሞ ሰለ "ሙስጠፋ ከማል "ታሪክ በደንብ ማወቅ አለባቸው ተብሎ በሳምንት አንዴ የታሪክ ክፍል አለን ማለት ነው። (ለ2 ሰሚስተር ብቻ)

በዚ ክላስ ታድያ አልፎ አልፎ የአለም ታሪክም እንማራለን።

ስለ አለም ታሪክ ሲያስተምሩ ታድያ ስለነበረው ቀኝ አገዛዝ አለማንሳት < የዶሮ ወጥ በልቶ የዶሮ ስጋ እንዳለመብላት ነው! > መቼስ...

ታዲያ መምህራችን ከአለም ሲኒማ የመጣ በሚመስል ትልቅ ስክሪን በቀኝ ግዛት የተያዙ ሀገሮችን ማሳየት ጀመረች....... የኔዋም ኢትዮጵያም; ከተያዙ ሀገር መድባ ማስረዳቷን ቀጠለች። ለምን ኣንድደሆነ ባላቅም <እንዴ..... > ከማለት ውጭ ምንም አላልኩም ነበር። የኔ ዝም ማለት ዝም ያላስባላቸው፤ አፍሪካውያን ዘመዶቼ ታዲያ... 'ቆይ ቆይ.... እዚጋ ስህተት አለ!' ብለው ስለታሪኬ ልክ እንደታሪካቸው አርገው ለክፍሉ ተማሪ እየተቀባበሉ አስረዱ።

…......

ከክላስ ቡሃላ ለምን ዝም እንዳልኩ ጠይቀውኝ..... ስለ አድዋ ድልም ትንሽ አውርተን ተለያየን። ከኔ በላነሰ መልኩ ስለ ስለ ሃገሬ ማወቃቸው... በተለይ ደሞ ስለ አድዋ ማወቃቸው የምር ነበር ደስ ያለኝ። ታዲያ አድዋ በየአመቱ ሲከበር ይህን ገጠመኜን መቼም አልረሳውም።

እውነትም አድዋ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያንም ድል ነው!


Comments


© 2023 by Jessica Priston. Proudly created with Wix.com

bottom of page