ጥያቄ እና መልስ?
- nejatahmedjuhar
- May 14, 2019
- 1 min read

«ዓለም ላይ ጥያቄ መጠየቅ የሚወድ ሕዝብ ማነው?» ቢሉኝ ያለማመንታት «ቱርክ» የምል ይመስለኛል። «አግብተሻል ወይ?» ብለው እንኳ ሳይጠይቁ «ባልሽ እድሜው ስንት ነው?» የሚሉ፣ አልያም «እናትሽ ሥራ ትሠራለች?» ብለው ከመጠየቃቸው በፊት «በወር ስንት ይከፈላታል?» ብለው የሚጠይቁ ሰዎች ያሉት ቱርክ ብቻ ይመስለኛል።
አንድ ቀን ታዲያ እንደተለመደው አንድ መሬም የምትባል የዶርም ጓደኛዬ ከፖሊስ ጋር የምኖር እስኪመስለኝ ድረስ ጥያቄ በጥያቄ እየደራረበች አታጣድፈኝ መሰላችሁ…!
«ነጁ!»
«ወዬ» አልኳት ከፈገግታ ጋር።
«አገራቹ ዩኒቨርሲቲ አለ?»
«አዎ።»
«ነጁ!»
«ወዬ!»
«የጫማ መጥረጊያስ አለ?» አለች ጫማዬን ስጠርግ ያየችበትን ቀን እያስታወሰች።
«ይቺን ይወዳል!!! አተተተተተ!!!!» ልል ፈለግኩና ተርጓሚ እንደማይኖር ትዝ ሲለኝ «ሆሆሆ! እንዴት የለም!? አለንጂ!» አልኳት በቁጭት ስሜት።
… ትንሽ ቆይታ ደግሞ ካውያ ስተኩስ አይታኝ መልሳ ወደጥያቄዋ ገባች።
«ካውያስ አላችሁ ነጁ?»
በቃ ልብሴን መተኮሴን ትቼ ካውያውን <ቢስሚላህ > ብየ ፊቷ ላይ ወርውሪው ወርውሪው አለኝ! ወዲያው ግን «አስተግፊሩላህ» አልኩና ራሴን እራሴን አረጋጋሁ። ከእኔ የባሰ ስንት የገጠማቸው ጓደኞቼ በሐሳቤ መጡብኝ። አንድ ከአፍሪካ የመጣ ጎደኛዬ ትዝ አለኝ። «ደምህ ቀይ ነወይ?» ብለው ጠይቀውት ነበር። እሱ እናቴ ችሎ አሳልፎታል። እኔስ ምን አናደደኝ እቴ! «አዎ ካውያም አለን» አልኳት በሰለቸ ስሜት። …
ያለ ዛሬ እንዳትጠይቂያት የተባለች ይመስል መሬም በጥያቄዋ ቀጠለች…
«ነጁ! አገራችሁ …… አለ?»
«አዎ አለ።»
«ነጁ......... አላችሁ?
«ውይይይ! አዎ አለ!»
…
«........ስ አለ?»
«አዎ አልኩሽ እኮ መሬም!»
«ውይ በጣም ይገርማል! እኔ ደግሞ የሌላችሁ መስሎኝ!»
«ቆይ ቆይ ግን መሬም!? ምን ነበር የጠየቅሽኝ አሁን? በደንብም ሳልሰማሽ ነው አዎ ያልኩሽ!»
«መንግስት አላችሁ ወይ ነበር ያልኩሽ።»
«ውይ እንደዚያ አትይም ታዲያ! ዌል እንግዲህ…! መንግሥት ላልሽው ጥያቄማ መልሱ .............. ነው እልሻለው።»
«ውይ እንዲያ ነው እንዴ!? ......ባንድ ፊቱ …… በይኛ!»
ማሳሰቢያ: (ባዶ ቦታውን የመሙላት ሙሉ መብት ለአንባቢው በሕግ የተጠበቀ ነው!!😀😀)
Comments