“ከስኬታማ ወንድ አጠገብ ስኬታማ ሴት አለች”
- nejatahmedjuhar
- May 14, 2019
- 1 min read

“ከስኬታማ ወንድ አጠገብ ስኬታማ ሴት አለች” የሚለውን አባባል የሰማቹ ከመቀመጫቹ ብድግ ብላቹ ያልሰሙ እህት ወንድሞቻቹን <ወንድ> የሚለውን <ሴት> በሚለው ቀይራቹ አሰሙ
ለምን ካላቹ ደግሞ ምክንያቴን እንደሚከተለው ልንገራቹ፦
ከዛ በፊት ግን አባባሉን ላልሰሙት አሰማቹ? ምን ነበር…….? “ከስኬታማ ሴት አጠገብ ስኬታማ ወንድ አለ” አዎ! ያለምንም ማንዛዛት……….
ሴት ልጅ መውለድ እንደነውር በሚታይበት ሃገር፤ ሴትን ልጅ ማስተማር ተራራን የመውጣት ያህል በከበደበት ሁኔታ፤ ሴትን ልጅ መደገፍ፡ ማበረታታት እንደ ኪሳራ የሚቆጥር ዜጋ ባለበት ሀገር፤ ሴትን መልከፍ በእናት ስም መሳደብ እንደባህል በሚቆጠርባት ኢትዮጵያ ላይ…. 1 ኣደለም 5 ሴቶችን እያሳደገ ያለውን አባቴን ማለትም አባት አለምን አንዴ ብቻ ልድገመው አባትዋዬን ካላደነቅኩ ካላመሰገንኩ ማንን አመሰግናለው?
የሴቶች ቀን (ቢያልፍም) የኔ(ኛ) ደጋፊ፣ ሞራል ሰጪ፣ አበረታቼ፣ ሴት ልጆች ስላሉት ብቻ ሳይሆን የሴት ልጅን ጥቃት ለማውገዝ ሰው መሆን በቂ ነው የሚለኝ ባባዬን…..
የምንፈልገውን እንድንማር የምንፈልገውን እንድንሰራ… ሴት ልጅ ወደ ጓዳ ሲባል አባባ የለም የለም ይህ እና መሰል አባባል ቤቴ ውስጥ እንዳይገባ ያለውን ጋሼን…
በሴት ልጆቹ የሚኮራ ፣ሴቶችን የሚደግፍ፣ ይህ የወንድ ስራ ነው…. ይህ ደሞ የወንዶች ትምህርት ነው…… የሚለውን ብሂል የምንፈልገውን የትምህርት አይነት የምንፈልግበት ቦታ ላይ እንድንማር በማድረግ አባባሉ ጊዜ እንዳለፈበት….. አውርተህ ሳይሆን አርገህ ስላሰየህ በአንድዬ ስም ምስጋናዬ ያለህበት ይድረስህ።
በመጨረሻም…
ለእረፍት ቤት በሄድኩበት ለአባቴ ስለ ኦፕራ ዌንፍሬ ያልነገርኩት ነገር የለም ኬት ተነስታ… የት እንደደረሰች፣ አሁን ላይ ምን እያረገች እንደሆነ፣ ብቻ ምን አለፋቹ ስለኦፕራ አጠር አርጌ(ያው አንድ ሁለት ሰአት ብቻ ሎል) ነገርኩት። እስክጨርስ ከሰማኝ ቡሃላ ለኦፕራ ያለውን አድናቆት ገልፆ ‘ኢትዮጵያዊት ኦፕራ ደግሞ የኔ ልጅ ነው ምትሆነው’ ብሎ ሞራል በሞራል አረገኝ እላቹሃለው። እና ምን ለማለት ‘የማይቻለው አይቻልም የሚለው ቃል ብቻ ነው።’ ባባ ነው ያለው…
መልካም ቀን!
Comentários