top of page

ይህን ያውቁ ኖሯል?

  • Writer: nejatahmedjuhar
    nejatahmedjuhar
  • May 14, 2019
  • 1 min read

•3 የስኳር ማንኪያ ደም አንድን ህፃን ልጅን ከሞት እንደሚታደግ ያውቃሉ? (ለማሙሽ እና ለሚጣ እንኵዋን እንኳ 3 ማንኪያ 3 ጭልፋ ደም ቢሰጥስ፧፦) • ኣንዴ ደም ሲለግሱ እስከ 7 ሰው ህይወት ለመትርፍ ምክንያት እንደሚሆኑስ? •አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ እስከ 1000 ሰው ህይወት መታደግ ይችላል። እንዴት? አትሉም…..ደም በመለገስ እላቹሃለው። (ለ1000 አይደለም ለአንድ ሰው እራሱ ሰበብ እንደመሆን ምን የሚያስደስት ነገር አለ?!) •በየቀኑ ሆስፒታል ከሚገቡ ሰባት ሰዎች አንዱ ደም ያስፈልገዋል። ይህ ማለት, በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የርሶን ደም ሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝተው ይጠብቃሉ ማለት ነው። •ደም ከለገሱ ቡህዋላ 650 ካሎሪ ይቃጠል ይላሉ ምሁራን። ( …እና ኪሎ ለመቀነስ የምታስቡ እህቶች ደም መለገስ ጥሩ ነው ስላቹ በታላቅ ደስታ እና ፍርሃት ነው። ደሞ በየሳምንቱ ካለገስኩ እንዳትሉ …) -እነ ቀጮም ደሞ አትፍሩ ደም ሰለለገስኩ እከሳ ይሆን እንዴ? የሚል ስጋት አይግባቹ….. ምክንያቱም በየ2 ወይም 3 ወር ልዩነት ነው ደም መለገስ የሚቻለው። እናማ.. ሰፊ የማገገሚያ ጊዜ አለ ለማለት ነው። ልጅ የሞለደች እናት እንኳ በሳምንታት ውስጥ ታገግም የለ እንዴ😉

*እንዲ ከሆነ እማ መች መለገስ ልጀምር ካላቹ..... እሁድ ታህሳስ 15 *የት ነው ቦታው? ለሚል…….. አዲስ አበባን ጨምሮ በአስር ከትሞች በሚገኝ የደም ባንክ *ይህን የመሰለ ፕሮግራም ማን አዘጋጀው? ለምትሉ ሙስተቅበል የልማትና መረዳጃ እድር

መልካም ቀን!

Comments


© 2023 by Jessica Priston. Proudly created with Wix.com

bottom of page